Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ነዋሪዎች የክተት ጥሪውን ተቀብለው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እንደሚያስከብሩ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድኖቹን ህወሓት እና ሸኔን አገር የማፍረስ ሴራ የሚያወግዝ ሰልፍ በጋምቤላ ከተማ ተካሂዷል።
በሰላማዊ ሰልፉ የሽብር ቡድኖቹን ድርጊት የሚያወግዙ እና የህልውና ዘመቻውን የሚደግፉ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
በሰልፉ የሽብር ቡድኑን ህወሓት ማስወገድ የኢትዮጵያን ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ ነው ፣ የሸኔና የወያኔ የጭካኔ እርምጃዎችን አጥብቀን እናወግዛለን፣ ወያኔ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ጠላት ናት፣ የሚሉ መፈክሮች ተስተጋብተዋል።
ሠልፈኞቹ በተጨማሪም ሸኔ እና ዘራፊው ወያኔ የሚያካሂዱት ሀገርና ህዝብን የማጥፋት ሴራ እኛ በህይወት እያለን ሊሳካ አይችልም ፣ የክተት ጥሪውን ተቀብለን በመዝመት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እናስከብራለን የሚሉ መፈክሮችን ማሰማታቸውን ከጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.