Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ ጎንደር ወደ ግንባር ከተተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ጎንደር ሕዝባዊ ሠራዊት የቀረበለትን የክተት ጥሪ ተቀብሎ ወደ ግንባር ከቷል።
የአማራ ሕዝብ የመኖር ሕልውና አደጋ ላይ ወድቋልና ለቀረበለት የክተት ጥሪ ፈጣን ምላሽ ሰጥቷል። ሕዝባዊ ሠራዊቱ የአማራ ሕዝብን አዋርዶ፣ ዘርፎና ገድሎ ኢትዮጵያን ለመበታተን የተነሳውን አሸባሪ ህወሓት ሳያጠፋ ወደ ቤቱ ላይመለስም ተማምሏል።
በመርኃ ግብሩ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ሲሳይ ዳምጤ፥ የሕልውና ዘመቻው የአማራ ክልልን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን እስከመጨረሻ ነጻ ለማውጣት እንደሆነ አብራርተዋል።
አቶ ሲሳይ እንዳሉት ጠላትን ማጥፋት የዘመቻው መዳረሻ ነው።
በሁሉም ግንባሮች ጠላት ዳግም በማያንሰራራበት ደረጃ ለመምታት ዝግጅት መደረጉን በመግለጽም መንግሥት ለዘማቾች አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ ቀለመወርቅ ምህረቴ በበኩላቸው ዘማቾች ታሪክ እየሠሩ ካሉት የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይል፣ የፋኖ፣ የሚሊሻ አባላት እና የአማራ ሕዝብ ጋር ተሰልፈው ተልዕኳቸውን በጀግንነት እንዲወጡም አስገንዝበዋል።
ሀገርን እና የአማራን ሕዝብ ነጻ ለማውጣት የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ተቋቁሞ በጽናት መዋጋትና ማሸነፍ ብቸኛው አማራጭ ነው ያሉት ደግሞ የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ ይርጋ ሲሳይ ናቸው።
የሁሉም ወረዳ የፖለቲካ መሪዎች፣ ሚሊሻዎች፣ የፖሊስ አባላት እና ልምድ ያላቸው ምልስ የሠራዊት አባላት የመሪነት ሚናውን በአግባቡ እንደሚወጡ ተናግረዋል።
የሚሰጡ መመሪያዎችን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ መልዕክት ማስተላለፋቸውን አሚኮ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
0
People reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.