በሀረሪ ክልል ለተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የሥራ ስምሪት ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል ለተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ቀጣይ ስራዎችን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ስምሪት ተሰጥቷል።
የሃረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በአገር አቀፍ ደረጃ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሻ በማድረግ ለምስራቅ ዕዝ ዋና መምሪያ እና ለምስራቅ ሀረርጌ ዞን በቅንጅት መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዩች ላይ ውይይት በማድረግ እና የሥራ መመሪያ በመስጠት ወደ ተግባር እንዲገቡ የሚያስችል አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት ÷አሽባሪው ህወሓት እና ተላላኪው ሸኔ አገር ለማፍረስ የሞት ሽረት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የጥፋት ቡድኑን እኩይ ተግባር ለማክሸፍ ኮሚቴው ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በትኩረት ሥራውን ማስፈጸም አለበት ብለዋል።
በተለይም የአሸባሪው ህወሃትና ሸኔ ሰርጎ ገቦችን የጥፋት ተልዕኮ ከማክሸፍ አንፃር የፀጥታ ሃይሉ ህዝብን ባሳተፈ መልኩ መስራት እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ከሃረሪ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በክልሉ የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ግብረ-ኃይል አባላትም የተሰጣቸውን ተልዕኮ በሙሉ ቁርጠኝነት ለማስፈጸም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!