የህወሓት እና ሸኔን እኩይ ተግባር እንደሚያወግዙ የገላን ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድኖቹን ህወሓት እና ሸኔን አገር የማፍረስ ሴራ የሚያወግዝ ሰልፍ በገላን ከተማ ተካሂዷል፡፡
በሰላማዊ ሰልፉ የሽብር ቡድኖቹን አገር የማፍረስ ሴራ የሚያወግዙ እና የህልውና ዘመቻውን የሚደግፉ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
በሰልፉ በሰብአዊ እርዳታ ሽፋን በአገራችን ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣውን ሴራ አንታገስም፣ ወያኔ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ጠላት ናት፣ እዘምታለሁ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አስከብራለሁ፣ በከሃዲዎች መቃብር ላይ የኢትዮጵያን ብልጽግና እናረጋግጣለን፣ የሽብር ቡድኑን ህወሓት ማስወገድ የኢትዮጵያን ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ ነው፣ የሸኔና የወያኔ የጭካኔ እርምጃዎችን አጥብቀን እናወግዛለን የሚሉ መፈክሮች ተስተጋብተዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!