የመዲናዋ ነዋሪዎች በምሽትና በቀን የአካባቢያቸውን ሰላም እያስጠበቁ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ነዋሪዎች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የአካባቢያቸውን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ እያስጠበቁ መሆኑ ተገለፀ፡፡
“እኔም የሰፈሬ ፖሊስ እና የሰላም ዘብ ነኝ” በሚል በከተማው በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና የወረዳው አመራሮች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት እና በመደራጀት በምሽት እና በቀን አካባቢያቸውን በንቃት በመጠበቅ ላይ ናቸው ተብሏል።
መላው የከተማው ነዋሪዎችም አካባቢዉን በንቃት በመጠበቅ የጀመረውን ተሳትፎ ይበልጥ በማጠናከር ለእኩይ ሴራ የተሰማሩ ፀጉረ ልውጦችንና ሰርጎ ገቦችን በመጠቆም እና በመያዝ ለአስተማማኝ ሰላም የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል መባሉን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!