Fana: At a Speed of Life!

የአገርን ህልውና ከማስጠበቅ ባሻገር በግብርናው ዘርፍ ክፍተት እንዳይፈጠር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ በዚህ አመት በአዲስ መልክ በሚተገበረው የተቀናጀ የግብርና ልማት ፕሮግራም ዙሪያ በሻሸመኔ ከተማ ውይይት አካሂዷል።

ቢሮው እንዳስታወቀው አሸባሪው ህወሃት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እያደረገ ያለውን ሴራ ከማክሸፍ ጎን ለጎን በግብርናው ልማት ዘርፍ ክፍተት እንዳይፈጠር በተቀናጀ መንገድ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ዘርፍ አስተባባሪና የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንዳሉት÷ አሁን በገጠመን ፈተና ምክንያት የግብርና ልማቱ እንዳይስተጓጎል ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት በልዩ ትኩረት ሊሰሩ ይገባል።

ግብርናውን ለማዘመን ሲተገበር የቆየው የግብርና እድገት ፕሮግራም የአርሶ አደሩን የአስተራረስ ዘይቤ፣ የኑሮ ሁኔታና ገቢ በማሳደግ በኩል ከፍተኛ ድርሻ እያበረከተ መሆኑን አቶ ኡስማን ተናግረዋል ።

ቀደም ሲል ሲተገበር የነበረው የግብርና እድገት ፕሮግራም በአዲስ መልክ የተቀናጀ የግብርና ልማት ፕሮግራም ተብሎ ሊጀመር እንደሆነ ማስታወቃቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የደቡብ ክልል ግብርና ልማት ፕሮግራም ሃላፊ አቶ ከድር መሀመድ እንዳሉት ፕሮግራሙ በክልሉ ከፍተኛ ባለባቸው 39 ወረዳዎችና 3 ልዩ ወረዳዎች በሚገኙ 948 ቀበሌዎች ተተግብሮ ውጤት እያመጣ ይገኛል ተብሏል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.