Fana: At a Speed of Life!

የሸኔና ህወሓት አገር የማጥፋት ሴራ በህይወት እያለን አይሳካም አሉ የባቢሌ ከተማ ነዋሪዎች

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገርን ለመታደግ ከሠራዊቱ ጎን ሆነው መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን የባቢሌ ከተማ እና ወረዳ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ ባካሄዱት ሰልፍ የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ ከመጠበቅ ባሻገር በተደራጀ መንገድ ለሠራዊቱ በማንኛውም መንገድ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ነው ባሰሙት መፈክር የገለጹት።

ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑ የባቢሌ ከተማ እና ወረዳ ነዋሪዎች ዛሬ በከተማው አሸባሪው ህወሓት በዜጎች ላይ እያደረሰ የሚገኘውን ጭካኔ የተሞላበት ተግባር በማውገዝ እና እስከ መስዋዕትነት ድረስ ለመክፈል መወሰናቸውን ገልጸዋል።

በሰልፉ ከሃዲዎች ህወሓትና ሸኔ በአገሪቱ እየፈጸሙ ያለውን ተግባር ለመመከት በአንድነት ለመዝመት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።

ህወሓት አገርን ለማፈራረስ የሚያራምደውን የሽብር አሉባልታዎች እና ከፋፋይ መረጃዎች በትክክለኛ መረጃዎች ከመመከት ባሻገር ግንባር ድረስ በመዝመት ለአገር ህልውና መስዋዕት ለመሆን ተዘጋጅተናል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.