ለቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ለቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ጥሪ አቅርቧል፡፡
በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን ሃገርን የማፍረስ ሴራ በማክሸፍ አገርን የማዳን ዘመቻ ላይ ባላቸው እውቀት ልምድ እና አቅም ከአገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመሰለፍ ይህ አፍራሽ ሃይል እስኪደመሰስ ድረስ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ባላቸው ተነሳሽነት ከሀገር መከላከያ ጎን በመቆም አቅማቸውና እውቀታቸው የፈቀደውን አስዋፅኦ ለማበርከት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
በዚሁ መሠረት ይህንን ተልዕኮ መወጣት የሚያስችል አካላዊ ሁኔታ ፣ የጤና ፣ የስነ – አእምሮ ዝግጁነት ፣ እውቀት እና ልምድ ያላቸውን አባላት ከዚህ በታች የተቀመጠውን መስፈርት ለሚያሟሉ የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የወጣ መስፈርት እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
1. አጠቃላይ መስፈርቶች
1.1. የኢፌዴሪ ሀገ – መንግስትን የተቀበሉ ፣
1.2. በህዝቦች ሉአላዊነትና አንድነት የሚያምኑ እና በፅናት ለማገልገል ሙሉ ፍቃደኝነት ያላቸው ፣
1.3. ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ የሆኑ ፣
1.4. በወንጀል ይሁን በፍታብሄር ተከሶ የፍርድ ቤት ክርክር የሌለባቸው
1.5. መከላከያ የሚያሰማራቸው የጦር ክፍሎች ሁሉ ተዘዋውረው ለመስራት ሙሉ ፍቃደኛ የሆኑና የአካል ብቃት ያላቸው ፣
1.6. ለእግረኛ አዋጊ መኮንኖች ፣ ሻለቃ አመራርና ከዚያ በላይ ሃላፊነት የነበራቸው ፣
1.7. በየትኛውም የማዕረግ ደረጃ ላይ በየማሰልጠኛ ማዕከላት አሰልጣኝ የነበሩ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
1.8. የሜካናይዝድ እና የቡድን መሳሪያ አመራርና ምድብተኛ የነበሩ ፣
1.9. የጤንነት ሁኔታን በተመለከተ
– የአይን ፣ የአፍንጫ ፣ የጆሮ ፣ የጥርስ ፣ የከንፈር ፣ ችግር የሌለባቸው ፣
– ከቲቢ ፣ ከሚጥል በሽታ ፣ ከስኳር ፣ ከደም ግፊት ፣ ከኪንታሮት ፣ከእንቅርት በሽታዎች ነፃ የሆኑ እና ለእንቅስቃሴ አስቸጋሪ የሆነ አካላዊ ችግር የሌለባቸው ( የማያነክስ ) ፣
1.10. የትምህርት ሁኔታ ማቀድ ፣ ማሠልጠን ፣ የስልጠና ዶክሜንት ማዘጋጀት የሚያስችል የትምህርት ዝግጅት ያለው፣
1.11. በሚመለመልበት አካባቢ ከቀበሌ ፣ ከመስተዳድር እና ከፖሊስ
ከወንጀል ነፃ ስለመሆናቸው የፅሁፍ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
1.12. የቀድሞ ጦር ሠራዊት አባል ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
2. ዕድሜን በተመለከተ፡-
2.1. ከወታደር እስከ ከፍተኛ የበታች ሹም ያሉ ከ55 ዓመት ያልበለጡ ፣
2.2. መስመራዊ መኮንኖች ከ60 አመት ያልበለጡ ፣
2.3. ከሻለቃ በላይ ያሉ ከፍተኛ መኮንኖች ከ64 ዓመት ያልበለጡ መሆን አለባቸው፡፡
3. የምልመላ ቦታና ጊዜ ፡-
-ለአዲስ አበባ ተመዝጋቢዎች በየክፍለ ከተማቸው ሲሆን
– ለክልል ተመዝጋቢዎች በየአካባቢያችሁ ባሉ የቀበሌ ፣ የወረዳ
አስተዳደርና የፀጥታ ወይም ሚሊሻ ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ መመዝገብ ይቻላል
– የምዝገባ ጊዜው ከህዳር 01 ቀን 2014 ዓ/ም እስከ ህዳር 15 ቀን 2014 ዓ/ም ድረስ ይሆናል፡፡
– በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች ዝርዝር መስፈርቶች ተለጥፎ የሚገኙ መሆኑ ተገልጿል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!