የሀገር ውስጥ ዜና

የክተት ጥሪውን በጠንካራ አደረጃጀት በመምራት አሸባሪው ህወሓትን ለመደምሰስ እየተሰራ ነው

By Feven Bishaw

November 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ያስተላለፈውን የክተት ጥሪ ተቀብሎ ወደ ግንባር የሚዘምተውን ሃይል በጠንካራ አደረጃጀት በመምራት አሸባሪውን ህወሓት ለመደምሰስ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ እንዳሉት፤ አሸባሪውን ህወሓት ለመደምሰስ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል ቁርጠኛ አቋም ተይዟል።