ቦርዱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሊያካሂድ የነበረውን ምርጫ ማቋረጡን አስታወቀ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በታህሳስ ወር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሊያካሂድ የነበረውን የምርጫ ሰሌዳን እና ዝግጅት ማቋረጡን አስታወቀ።
ቦርዱ 6ኛው አጠቃላይ ምርጫን በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች አከናውኖ ያጠናቀቀ ሲሆን በቢኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ደግሞ በታህሳስ ወር ምርጫውን ለማከናወን የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ ተግባራትን ማከናወን ጀምሮ እንደነበር ይታወቃል።
ይሁን እንጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀውን አገር አቀፍ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ትናንት ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ማጽደቁን ተቀትሎ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምርጫ ሰሌዳን እና ዝግጅትን ያቋረጠ መሆኑን አስታውቋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

0
People reached
0
Engagements
–
Distribution Score
Boost Post
Like
Comment
Share