Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እና ዩጋንዳን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዓለምፀሐይ መሠረት ከዩጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲኤታ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው የሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ምክክር ማድረጋቸው ተገልጿል።
በተለይም በአገራቱ መካከል ስላለው የንግድ ግንኙነት ስለሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርገው ተወያይተዋል።
በተጨማሪም አምባሳደር ዓለምፀሐይ በአገራችን ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ገለፃ አድርገዋል።
ዩጋንዳና ኢትዮጵያ በተለያዩ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ መድረኮች ላይ ተመሳሳይ አቋም የሚያራምዱ፣ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
No photo description available.
0
People reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.