Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መሳሪያ የታጠቀ አካል እንዲያስመዘግብ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የጦር መሳሪያ የታጠቀ ማንኛውም አካል እንዲያስመዘግብ የክልሉ መንግስት ጥሪ አቀረበ፡፡
በክልሉ መሳሪያ የታጠቀ ማንኛውም አካል ከጥቅምት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ሊያስመዘግብ ይገባል ነው የተባለው፡፡
የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ መለሰ÷ በክልሉ መሳሪያ የታጠቁ ማንኛውም አካላት መሳሪያቸውን በማስመዝገብና ሕጋዊ በማድረግ ለአገራዊ የክተት ጥሪው የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
መሳሪያ እያላቸው በተጠቀሱት ቀናት በማያስመዘግቡ አካላት ላይ አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም ገልጸዋል።
የቀድሞ ሃገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከዚህ ቀደም በክልሉ የጸጥታ አካላት የነበሩና በክብር የተሠናበቱ፣ እንዲሁም መላው የክልሉ ሕዝብም በተደራጀ መልኩ አካባቢውን በመጠበቅ ለአገራዊ የክተት ጥሪው ዝግጁ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
እንደ ሃገር የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአግባቡ ለመተግበር አደረጃጀት ተፈጥሮ ወደሥራ መገባቱን ጠቁመው÷ የክልሉ ሕዝብ ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ትግበራ መሳካት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም መጠየቃቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.