Fana: At a Speed of Life!

አንድነታችንን በማጠናከር ከመከላከያ ጎን መቆም ይኖርብናል – አቶ ተስፋዬ ይገዙ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 26፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን ፈታኝ ምዕራፍ ላይ በመሆናችን ሁሉም መሪ በመሆን፣ ህዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠርና አንድነትን በማጠናከር ከመከላከያ ጎን መቆም ይኖርበታል ሲሉ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ አሳሰቡ፡፡
ፈታኝ ሁኔታዎችንና መሸጋገሪያችን በሚል ርዕሰ ጉዳይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ሃገራችን በውስጥና በውጭ ጠላቶች እየተፈተነች ትገኛለች ብለዋል፡፡
የጠላት ሃይሎች ትልቁ እቅዳቸው ኢትዮጵያን ማፈራረስ እና ኢትዮጵያውያንን አንገት በማስደፋት በአንባገነንነት መግዛት ነው ሲሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡
የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ አቅሙን በማጎልበት የበላይነትን ለመያዝ የሚቋምጠው አሸባሪው ህዋሓት የሃገር መከላከያ ሰራዊቱን በማፍረስና የራሱን የጸጥታ ሃይል በማደራጀት ኢትዮጵያን በራሱ ሰዎች እንዲመሩ በማድረግ ለሩብ ክፍለ ዘመን ሃገሪቱን ሲዘውራት ነበር ብለዋል፡፡
ከመነሻው በሶስት ምዕራፍ ዝግጅት ያደረገ ሲሆን የመጀመሪያው ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ሠራዊቱን በማፍረስ፣ የሰሜን ዕዝ ላይ አሰቃቂ ድርጊት በመፈጸምና መንግስት ሆኖ መቐለን ከተቆጣጠረና ጫካ ከገባ በኋላ ከፍተኛ ፕሮፖጋንዳ በመስራት የትግራይን ህዝብ ወደ ጦርነት እንዲገባ አድርጓል ነው ያሉት፡፡
ፍላጎቱም ተከበናል በማለት የታጠቀና ያልታጠቀ፣ በየትኛውም ደረጃ ወደ ጦርነት እንዲገባ በማድረግ ኮሪደሮችን በማስከፈት በመደራደርና የሚፈልገውን ነገር ለማስፈፀም አስቦ መንቀሳቀሱን ገልፀዋል፡፡
ነጻነታችን የትግላችን ውጤት ነው ያሉት አቶ ተስፋዬ ለመከላከያ ሃይላችን ሙሉና ልባዊ ድጋፍ ማድረግ አለብን ማለታቸውን ከደቡብ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.