ሕብረተሰቡ የጥፋት ሃይሎችን ማጋለጥ እንጂ በጉያው ስር መደበቅ የለበትም – የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 26፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕብረተሰቡ የጥፋት ሃይሎችን ማጋለጥ እንጂ በጉያው ስር መደበቅ የለበትም ሲሉ የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አዱኛ አሕመድ ተናገሩ።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ባጸደቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስፈላጊነትና የአተገባበር ሁኔታ ላይ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሃላፊ ወይዘሮ አዱኛ አሕመድ የሰጡ ሲሆን፥ ሕብረተሰቡ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስፈላጊነት በአግባቡ መገንዘብ፣ አዋጁን መተግበር፣ አዋጁ እንዲተገበር መተባበርና ማገዝ ይኖርበታል ብለዋል።
ሕብረተሰቡ የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥና የሃገር ሉዓላዊነትን በማስከበር ሂደት ውስጥ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ያሉት ሃላፊዋ ማንም ሰው ከጥፋት ሃይሎች ጋር በምንም አይነት መንገድ መተባበር የለበትም ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!