Fana: At a Speed of Life!

አፍርሼ እረማመድባታለሁ” ብሎ የተነሳውን አሸባሪ ቡድን በጋራ ክንዳችን እናፈርሰዋለን-ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)”ኢትዮጵያን አፍርሼ እረማመድባታለሁ” ብሎ የተነሳውን አሸባሪ ቡድን በጋራ ክንዳችን እናፈርሰዋለን ሲሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ተናገሩ።

ኢትዮጵያዊያን ለ27 አመታት ግፍና በደሉን ተሸክመው ቆይተው መከራው ሲበረታባቸው “በቃህ” ብለው ያስወገዱት አሸባሪው ህወሃት “ኢትዮጵያን ሳላፈርስ ወደ ሲኦል አልገባም” በማለት የቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ይገኛል።

የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያን በበላይነትና በፍፁም አምባገነናዊነት በመራባቸው ዓመታት በዜጎች ላይ አስቦ ያልፈፀመው ክፋትና በደል አልነበረም።

የህወሃት አሸባሪ ቡድን “እኔ የማልመራት ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት” በማለት አገርና ድንበር ጠባቂ ሰራዊት በማጥቃት ክህደቱን አሳይቷል።
አሸባሪው በፈፀመው ወንጀል መንግስት ተገዶ ወደ ህግ ማስከበር በገባበት ወቅት ወደ በርሃ ተበታትኖ የነበረው ሃይል ቆይቶ መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም በማድረጉ እንደገና ተሰባስቧል።

ቡድኑ ከተሰባሰበ በኋላም ከህፃናት እስከ አዛውንት ለጦርነት አሰልፎ በአማራ እና አፋር ክልሎች ወረራ በመፈፀም ንጹሃንን በመግደል፣ የቤት እንስሳትን ጨምሮ ንብረት በመዝረፍና በማውደም የጭካኔ ተግባሩን አሳይቷል።

በመሆኑም “ኢትዮጵያን አፍርሸ እረማመድባታለሁ” ብሎ የተነሳውን አሸባሪ ቡድን በጋራ ክንዳችን እናፈርሰዋለን ሲሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ገልጸዋል።

የሽብር ቡድኑ ከንቱ አላማ መቼም ቢሆን የማይሳካ ነው ያሉት ዶክተር ቢቂላ፤ የኢትዮጵያ ልጆች ከንቱ ህልሙን አምክነው መዳረሻውን “ሲኦል” ያደርጉታል ነው ያሉት።

ከኢትዮጵያ ሁሉም ማእዘናት በመንቀሳቀስ ”በደምና በአጥንቴ መስዋዕትነት ከፍዬ የማድናት እኔ ነኝ” በማለት አሸባሪውን እየተፋለሙት መሆኑን ዶክተር ቢቂላ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በጠላት ላይ በጋራ መነሳትና መዝመት የኢትዮጵያዊያን መገለጫ መሆኑን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅትም የኢትዮጵያን ህልውና ለማስጠበቅ ሁሉም ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.