የሀገር ውስጥ ዜና

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከ3 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን ነገ ያስመርቃል

By Feven Bishaw

November 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከ3 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ነገ እንደሚያስመርቅ የዩኒቨርስቲው የዓለምአቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አስታወቁ።

ዩኒቨርሲቲው ለ13ኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ከሚስመርቃቸው ተማሪዎች መካከል 1 ሺህ 6ቱ ሴቶች ናቸው።