Fana: At a Speed of Life!

የሲኤንኤን ዘገባ በኡጋንዳ ጋዜጠኛ ሲጋለጥ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 26፣2014 (ኤፍ ቢሲ)ስለ አዲስ አበባ በሲኤንኤን የሰማሁትና ቦታዉ ደርሼ ያየሁት የተለያዩ ናቸዉ ሲል ኡጋንዳዊዉ ጋዜጠኛ ዳንኤል ሉታያ ተናገረ፡፡
ወደ አዲስ አበባ በረራ ከማድረጌ በፊት ከሲኤንኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደሰማሁት ወደ ጦርነት ቀጠና የምሄድ መስሎኝ ነበር ነገር ግን እዉነታዉ ሌላ ሆኖ ነዉ ያገኘሁት ብሏል ጋዜጠኛዉ፡፡
ትላንት አዲስ አበባ አሁን ደግሞ አዳማ እንደሚገኝ የሚገልፀው ጋዜጠኛው በሄደበት ቦታ ምንም የፀጥታ ችግር አለመኖሩን ገልጿል።
የጥይት ድምፅ የለም፤ ውጥረት የለም፣ ባር ቤቶች ክፍት ናቸው ፣የተዘጋም መንገድ የለም ብሏል።
ዜጎች የተለመደዉን የእለት ከእለት ስራቸዉን እያከናዎኑ መሆኑንና የፀጥታ አካላትም በከተማዋ ተሰማርተዉ በስራ ላይ መሆናቸዉን ተናገሯል፡፡
በኡጋንዳ ካምፓላ የሚገኘዉ የኤንቢኤስ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ የሆነዉ ዳንኤል ሉታያ በአፍሪካ የፖለቲካ ጉዳዮችን፣ዲፐሎማሲንና ድንበር ተሻጋሪ ግጭቶችን በተመለከተ ትንታኔ በመስጠት ይታወቃል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.