የወያኔና የሸኔ ጥምረት የሚቀጥለው የወያኔን የበላይነ መሸከም እስከቻለ ጊዜ ድረስ ብቻ ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወያኔና ሸኔ ያላቸው ጥምረት የሚቀጥለው የወያኔን የበላይነትና የገዥነት ባህሪ መሸከም እስከቻለ ጊዜ ድረስ ብቻ ነው ሲሉ አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ።
አቶ ሽመልስ ከኦቢኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ እብሪተኛው ወያኔ የኦሮሞን አቅም ስለሚያውቅ በኦሮሞ ላይ ትኩረት አድርጎ በመንቀሳቀስ ባለፉት 27 ዓመታት የራሱን የበላይነት ለመጫን ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
ወያኔ በኦሮሞ ፖለቲካ ላይ አተኩሮ የሰራውም በመጀመሪያ የራሱን የበላይነት በሌሎች ላይ በመጫን፥ ሌሎች ህዝቦች የበታችነትን እንዲቀበሉ ለማድረግ ነው ብልዋል አቶ ሽመልስ።
27 ዓመታት ሙሉ የኦሮሞን ሀብት በመዝረፍ ፥ ህዝቡም ሆነ የኦሮሞ ልጆች ጥያቄና የተለየ ሀሳባ እንዳየነሱ ማድረግ ዋነኛው ዓላማው እንደነበረም ገልጸዋል።
የህዝቡን ትግል በስርዓት ለመምራት የሚችል ብቁ አመራር እንዳይወጣና የኦሮሞ ትግል ፍሬ እንዳያፈራ ሲያደርግ መቆየቱንም ነው አቶ ሽመልስ ያብራሩት ።
አሸባሪው ህወሃት በህዝባችን ጫንቃ ላይ ይህንን የበላይነትና የገዥነት ባህሪ ሲጭን የኖረው በሀሰተኛ ፌደራሊዝም ስም ሲነግድ መኖሩንም አስረድተዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!