Fana: At a Speed of Life!

ጀግኖቻችንን ማበረታታትና ከጎናችሁ ነን ማለት ከሁሉም ዜጋ ይጠበቃል -ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በሀገር መከላከያ ጦር ኮሌጅ በመገኘት በህልውና ዘመቻው ጉዳት የደረሰባቸውን የሠራዊት አባላትን ጎበኙ ፡፡

ከንቲባዋ የምግብ ቁሳቁስ እና የተለያዩ የአልባሳት ድጋፍም አድርገዋል።

ከንቲባዋ ጀግና የመከላከያ ሰራዊታችን አባላት ለኢትዮጵያ ክብር ሲሉ የከፈሉት የአካልና የህይወት መስዋዕትነት የእያንዳንዳችን ተከፍሎ የማያልቅ ዕዳ ነው ብለዋል ።

በህልዉና ጦርነቱ የተጎዱ ጀግኖች ተጎድተው እንኳን በገፅታቸዉ ላይ የሚታየዉ እልህና ኢትዮጵያዊ የአይበገሬነት ስሜት አስደናቂ ነዉ ሲሉም ገልፀዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎች በተለያዩ ካምፖች በመሄድ በህልውና ዘመቻው የጀግንነት ተግባር ፈጽመው ጉዳት የደረሰባቸውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በመጠየቅ እንዲያበረታታ እና ድጋፍ እንዲያደርጉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ እና ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች በኮሌጁ ለሰራዊቱ አባላት የህክምና ድጋፍ በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ከንቲባዋ መግለፃቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.