Fana: At a Speed of Life!

በአጭር ጊዜ ውስጥ ሽብርተኛውን ወራሪ ኃይል ማጥፋት አለብን – ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተናበበ ሕዝባዊ ማዕበል በመዝመት፣ አካባቢን ከጠላት ተላላኪ ነቅቶ በመጠበቅ እና ለወገን ጦር የሚደረገውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማጠናከር በአጭር ጊዜ ውስጥ ሽብርተኛውን ወራሪ ኃይል ማጥፋት አለብን አሉ ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ።
የአማራ ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ አሁን ላይ ሽብርተኛውና ወራሪው ህወሃት ራሱ በቀቢጸ ተስፋ በአማራ እና በአፋር ሕዝብ ላይ በከፈተው ወረራ በገባበት መንገድ መውጣት እንደማይችል አውቋል ብለዋል፡፡
አሸባሪው ኃይል በተስፋ መቁረጥ እየወሰዳቸው ያሉት ርምጃዎች ይህንን አመላካች መሆናቸውን ጠቅሰው፥ ወራሪው ቡድን ድጋሜ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሕልውና ሥጋት በማይሆንበት ደረጃ ማጥፋት የግድ መሆኑን ነው የልዩ ኃይል አዛዡ የገለጹት፡፡
የሽብርተኛውን ወራሪ ኃይል እንቅስቃሴ ለመግታትና የወረራቸውን አካባቢዎች ነፃ ለማውጣት ከመደበኛው የመከላከያ ሠራዊት በተጨማሪ ሕዝባዊ ማዕበል ያስፈልጋል ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ፥ ለዚህም ሲባል በመንግሥት በኩል የክተት ጥሪ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
“ዛሬ የተረከብናትን እና የምንኖርባትን ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት የነፃነት ማማ የክብር ቦታ ላይ ያገኘናት ያለ ዋጋ አይደለም” ያሉት ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ፥ የአሁኑ ትውልድም የአባቶቹን ውርስ ማስጠበቅ እንደሚኖርበት አሳስበዋል።
በክተት ጥሪው መሠረት የሥራ ኃላፊዎች እና ሕዝቡ በቅንጅት እየሠሩ በመሆኑ ወራሪውን ኃይል በወረረው መሬት ላይ ሳንቀብር አንመለስም ነው ያሉት።
ሽብርተኛው የህወሃት ቡድን የያዘው ጭፍጨፋ፣ ዝርፊያ እና ውድመት የሚመከተው በተናበበ ሕዝባዊ ማዕበል መሆኑንም ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ገልጸዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.