የኢትዮጵያን ህልውና ጠብቆ በማቆየት ረገድ የሴቶች ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ህልውና ጠብቆ በማቆየት ረገድ የሴቶች የላቀ ሚና አሁንም ተጠናክሮ እንደሚቀየኢትዮጵያን ህልውና ጠብቆ በማቆየት ረገድ የሴቶች ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ህልውና ጠብቆ በማቆየት ረገድ የሴቶች የላቀ ሚና አሁንም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመለከተ።
ከአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ከ1 ሺህ በላይ ሴቶች የተሳተፉበት በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሃና የሺንጉስ፤ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በማስጠበቅ የሴቶች ጀግንነት የላቀ መሆኑን አስታውስዋል።
በኢትዮጵያ ታሪክ፥ ሴቶች በተለያዩ የጦር አውደ ግንባሮች ተሰልፈው ድል በማድርግ፣ ስንቅ በማቀበል፣ ጦር በመምራትና በማበረታታት ጭምር ተነግሮ የማያልቅ ጀብድ ፈፅመዋል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያን ህልውና ጠብቆ በማቆየት ረገድ የሴቶችን የላቀ ሚና ጠቅሰው አሁንም ለኢትዮጵያ ህልውና እየተዋደቁ ያሉ በርካታ ጀግና ሴቶች መኖራቸውን ገልጸዋል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ሜሮን አረጋው በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ በአሸባሪው ህወሃት የተጋረጠባት ችግር በጀግኖች ልጆቿ ትግል ይቀለበሳል ብለዋል።
በመድረኩ የተገኙ ሴቶች እንዳሉት፥ የከተማዋን ብሎም የኢትዮጵያን ህልውና፤ ሰላምና መረጋጋት ለማስጠበቅ የሴቶች ሚና ወሳኝ ነው።
ሴቶች በጦር አውድማዎች ላይ ከመሪነት ጀምሮ የተለያዩ ሚናዎችን ሲወጡ መቆየታቸውን አውስተው፥ አሁንም እየተካሄደ ባለው የህልውና ዘመቻ ሴቶች ጀግንነታቸውን በተለያየ መንገድ እያሳዩ መሆናቸው ተገልጿል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!ጥል ተመለከተ።

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!