የሀገር ውስጥ ዜና

የአሸባሪዎቹን ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ ሰልፍ በሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

November 06, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪዎቹን የህወሓትና የሸኔን ሀገር የማፍረስ ድርጊትን የሚያወግዝ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ።

በሰልፉ በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ሰልፈኞቹ የአሸባሪዎቹን የህወሓትንና የሸኔን ሀገር የማጥፋት የጭካኔ ድርጊቶችን በአንድነት እንመክታለን! ኢትዮጵያ የምትሸነፍ ሀገር አይደለችም !

አከባቢዬን እጠብቃለሁ ሀገሬን ለማዳን እዘምታለዉ!

ሁላችንም በጋራ የጥፋት ሀይሎችን ልንመክታቸዉ ይገባል !

የትህነግን ተልዕኮ የሚያስፈፅሙ በየአካባቢው ተሰግስገው የሚገኙ ባንዳዎችን በማጋለጥ የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ።

በጀግኖቻችን ደምና አጥንት የተገነባች ሀገር በአሸባሪዎቹ የህወሓትና ሸኔ እኩይ ድርጊት አትፈርስም ።

በከሀዲዎች መቃብር ላይ የኢትዮጵያን ብልጽግናን እናረጋግጣለን የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት ላይ ይገኛሉ ።

በአበበች ኬሻሞና በኢብራሂም ባዲ

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!