Fana: At a Speed of Life!

የትህነግንና የሸኔን ኢትዮጵያን የማፍረስ ህልም ለማምከን ዝግጁ መሆናቸውን የምዕራብ አርሲ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሸብርተኞቹን የትህነግና የሸኔን ኢትዮጵያን የማፍረስ ዓላማና ህልም ለማምከን ዝግጁ መሆናቸውን የምዕራብ አርሲ ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ።

የምዕራብ አረሲ ዞን ነዋሪዎች በነጌሌ አርሲ ከተማ የትህነግንና የሸኔን ሀገር አፍራሽ የጥፋት እንቅስቃሴ በማውገዝ ለሀገር ሉዓላዊነት በመዋደቅ ላይ ላሉት ለሀገር መከላከያ፣ ለፀጥታና ለህዝባዊ ሰሠራዊት አካላት ያላቸውን ድጋፍ በሰልፍ በመግለጽ ላይ ናቸው።

በዚህ ሰልፍ ላይ ከዞኑ 13 ወረዳዎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

በሰልፉ ላይ “የሀገር መከላከያ ሰራዊት አለኝታችን ነው! ህወሃትና ሸኔ የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸዉ! መከላከያችንን በመቀላቀል የሀገራችንን ህልውና እናስከብራለን! እኛ እያለን ሀገራችን በእኩይ ግለሰቦች አትፈርስም! ህወሃትና ሸኔ የሀሉም ኢትዮጵያዊ ጠላት ናቸው ! “ የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች ተሰምተዋል።

የሰልፉ ተሳተፊዎች በዚሁ ጊዜ በሰጡት አስተያየት፥ አሸባሪው የወያኔ ቡድን እኔ ካልመራኋት ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት ብሎ የክፋት በትሩን እንዳነሳ ገልጸው፤ ይህ ሀሳቡ ግን ኢትዮጵያውያን እያለን መቼም አይሳካለትም ብለዋል።

እኛም በተባበረ ክንድ የጁንታውን ህልም ከንቱ ለማድረግ ለመከላከያ ሰራዊትና ለሌሎቹም የፀጥታ ሃይሎች የምናደርገውን ድጋፍ በማጠናከርና በግንባርም በመዝመት የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ወያኔ በስልጣን ላይ በነበረበት ዘመንም ህዝብን በመከፋፈል እርስ በርሱ እንዲጠራጠር በማድረግ የኢትዮጵያን ልጆች ደም ሲመጥ ነበር ያሉት ነዋሪዎቹ፥ የኦሮሞ ህዝብም ልክ እንደሌሎቹ ወንድሞቹና እህቶቹ ሀሉ ልጆቹን ሲገብርና ዋጋ ሲከፍል የኖረው በወያኔ ዘመን መሆኑን አውስተው ፥ ይህ ቡድን ተመልሶ የመግዛት እድል እንዲኖረው በፍፁም አንፈቅድለትም ብለዋል።

ሀገራችን ስትፈርስ ዝም ብለን የምናይበት ህሊና የለንም የሚሉት ነዋሪዎቹ ፥ የጨፍጫፊው የህወሓት ተላላኪ የሆነው ሸኔ በኦሮሞ ህዝብ ስም ሀገር ለማፍረስ መነሳቱ አሳፋሪ ነው፥ የኦሮሞ አምላክ የእጃቸውን ይሰጣቸዋል ብለዋል።

የምዕራብ አርሲ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ሀጂ፥ ትህነግ ባለፋት አመታት ስልጣኑን መከታ በማድረግ በኢትዮጵያ ህዝብና በኦሮሞ ህዝብ ላይ የፈጸመው ግድያና በደል አልበቃ ብሎት ፥ አሁንም እያካሄደ ያለው ወረራ፥ ዝርፊያና ጭፍጨፋ ይቅር የማይባልና በአንድነት ትግላችን የምንቀለብሰው ነው ብለዋል።

አክለውም ሀገር አልባ ላድርጋችሁ እያሉ ለሚገኙት ሸኔና ትህነግ እድል መስጠት የለብንም ፥ ወደ ግንባር ዘምተን መከላከያን ደግፈን ሉዓላዊነታችንን ማስከበር አለብን ነው ያሉት።

የምዕራብ አርሲ ዞን ሀደ ሲቄዎችና አባገዳዎች የኦሮሞ ህዝብ ለኢትዮጵያ አንድነት ከጥንት ጀምሮ የከፈለውን መስዋዕትነት አሁንም ጁንታና ሸኔን በመዋጋት ታሪኩን ማደስ፥ አካባቢውን ከሰርጎገቦችና አስመሳዮች መጠበቅና አንድነቱን ማጠናከር አለበት ብለዋል።

ጥላሁን ይልማ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.