ህወሓት በአገር ህልውና ላይ የደቀነውን አደጋ በተባበረ ክንድ መቀልበስ አለብን – የኢዜማ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ሕወሓት በአገር ህልውና ላይ የደቀነውን አደጋ ሁሉም ወገን በተባበረ ክንድ መቀልበስ እንደሚኖርበት የኢዜማ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ አመለከቱ፡፡
ፓርቲው አባላቶቹና ደጋፊዎቹ ወደ ግንባር እንዲዘምቱና ለትግሉ ድጋፍ እንዲያደርጉም የበኩሉን እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡
አቶ ናትናኤል ፈለቀ ለኢፕድ እንደገለጹት ÷ በአሁኑ ጊዜ አሸባሪው ህወሓት በአገር ህልውና ላይ ፈርጀ ብዙ አደጋዎችን ደቅኗል፡፡
ቡድኑ የኢትዮጵያን ህዝብ የመኖር ዋስትና እየተፈታተነ እንደሚገኝ የገለጹት ሃላፊው÷ የኢትዮጵያ ህዝብ የመኖር ዋስትናውንና የሀገሩን ህልውና ለማረጋገጥ ሁሉም ወገን በተባበረ ክንድ አሸባሪውን ህወሓት ማስወገድ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ቢኖራቸውም ለጊዜው ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው በሀገር ጉዳይ ላይ በጋራ መስራት እንዳለባቸው አመላክተው ÷ የፖለቲካ አመለካከትን በነጻነት ማራመድ የሚቻለው አገር ስትኖርና ሰላም ሲሰፍን መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!