Fana: At a Speed of Life!

በዲላ ከተማ ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በሰልፉ ላይ ህዝቡ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ያለውን ድጋፍ በተለያዩ መፈክሮች ገልጿል።

አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እያደረገ ያለውን ጦርነት ለመመከት ከመከላከያ ጎን በሁሉም ዘርፍ ለመቆም መዘጋጀታቸውንና ከዚህ በፊትም የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል ።

ጁንታው የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር እያደረገ ያለው ደባ እንዳሳዘናቸው በሰልፉ የተሳተፉ የከተማው ነዋሪዎች ገልጸዋል ።

ኢትዮጵያን ለማዳን ሁሉም በየችሎታው መዝመት እንደለበትም ነው የገለጹት ።

በሰልፉ ‘‘አካባቢየን እጠብቃለሁ ፤ ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ ፤ ታላቁ የለውጥ ጉዞዎችን በውስጥና በውጪ ጠላቶች አይደናቀፍም ፤የአሸባሪው ህወሓት ተስፋ በትግላችን እናመክናለን ፤ ለፕሮፖጋንዳ ጦርነት አንበረከክም’’ እና የመሳሰሉት መፈክሮች ተስተጋብተዋል ።

በማስተዋል አሰፋ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.