የውጭ ሃይሎች ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት እንቃወማለን – የጎባ ነዋሪዎች
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ሃይሎች ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና ጫና አጥብቀው እንደሚቃወሙ በባሌ ዞን የጎባ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ገለጹ።
ነዋሪዎቹ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍና የውጭ ኃይሎች ጫናን የሚያወግዝ ሰልፍ በጎባ ከተማ አካሄደዋል።
የአሸባሪውን ህወሓት የጥፋት ሴራ በማክሸፍ የአገር ህልውናን ለማስከበር አስፈላጊውን መስዋዕትነት እንደሚከፍሉም አስታውቀዋል፡፡
መከላከያችን የሉዓላዊነታችን ዓርማ ነው፣ ሉዓላዊነታችንን በደምና አጥንታችን እናስከብራለን ፣ አሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ የኢትዮጵያውያን ጠላት ናቸው ብለዋል ነዋሪዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት።
የከተማዋ ነዋሪዎች የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነትን በመቃወም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ጠይቀዋል፡፡
አሸባሪዎችና የውጭ እጅ አዙር ቅኝ ገዥዎች እያደረሱብን የሚገኘውን ጫና በአንድነት በመመከት ህልውናችንን ማረጋገጥ አለብን ብለዋል፡፡
ያልተረጋገጠ ወሬ የሚነዙ የአሸባሪውን ተላላኪዎች በማጋለጥ ለህልውና ዘመቻው ስኬት የድርሻውን እንደሚወጣም ገልጿል፡፡
ወይዘሮ ስቲና መሐመድ በበኩላቸው ለህልውና ዘመቻው ስኬት ከዚህ በፊት ስንቅ በማዘጋጀትና የወር ደመወዛቸውን በመለገስ አጋርነታቸውን ማሳየታቸውን አስታውሰዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሀገሪቱን ዳር ድንበርና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ እየተካሄደ ያለው የህልውና ዘመቻን ለማሳካት የሚበጅ በመሆኑ ስራ ላይ እንዲውል እንደሚደግፉ ነዋሪዎቹ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል፡፡
የባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሀኪም አልይ ፤ የጎባ ከተማና አካባቢው ነዋሪ ህዝብ አሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔን ለማውገዝ ሰልፍ ማድረጉ ለአገሩ ያለውን ክብር የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሀገርን ለማደን እየተካሄደ ያለው ዘመቻ በድል እስኪጠናቀቅ ድረስ ህዝቡ ሁለንተናዊ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በተመሳሳይ የውጭ ጣልቃ ገብነትንና አሸባሪዎቹን የሚቃወም ሰልፍ በምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ ተካሄዷል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!