በሀዲያ ዞን ህወሓትን የሚያወግዝና ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ሠልፍ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀዲያ ዞን የአሸባሪውን የህወሃት ሴራ የማሚያወግዝና ጀግናውን መከላከያ ሠራዊት የሚደግፍ ሠልፍ እየተካሄደ ይገኛል።
የሠልፉ ተሳታፊዎች የአሸባሪውን ህወሓት የሽብር ተግባር እያወገዙ እንደሚገኙ ደሬቴድ ዘግቧል።
በሰልፉም ‘’ሀገሬን እጠብቃለሁ መስዋዕትነትን እከፍላለሁ፤ በእኛ መስዋዕትነት ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች ፤ አከባቢህን ጠብቅ ፤ ወደ ግንባር ዝመት፣ ልማቱን እቀጥላለሁ ፤ የኢትዮጵያ ጠላቶችን እፋለማለሁ፤ ለቀረበልን የክተት ጥሪ በህዝባዊ ቁጭትና ጽናት እታገላለሁ’’ የሚሉና የመሳሰሉ መፈክሮችን እያስተጋቡ ይገኛሉ።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!