Fana: At a Speed of Life!

ኦሮ-ፍሬሽ አክሲዮን ማህበር የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶችን ለመዲናዋ ነዋሪዋች ማቅረብ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘ኦሮ-ፍሬሽ’ የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ አክሲዮን ማህበር ዛሬ የተለያዩ የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶችን ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ ማቅረብ ጀመረ።

አክሲዮን ማህበሩ አምራቹን ቀጥታ ከሸማቹ ጋር ለማገናኘት የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለአዲስ አበባ ገበያ እንደሚያቀርብ መግለጹ ይታወሳል።

በዛሬው እለትም በአዲስ አበባ ሳር ቤት የአትክልትና ፍራፍሬ ሽያጭ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል።

አላማው አምራቾች በቀላሉ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን በቀጥታ ለሸማቹ ህብረተሰብ ለማድረስ ያለመ ነው ተብሏል።

ተቋሙ ምርቱን ለሸማቹ በቀጥታ በማቅረብ የገበያ ሰንሰለትን ማሳጠርና ገበያን የማረጋጋት ዓላማዎችን ይዟል።

የኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን፣ መቂ ባቱ አትክልትና ፍራፍሬ ህብረት ስራ ዩኒየን እና ሌሎች ህብረት ስራ ማህበራት ተሳትፈዋል።

ገበያውም ቅዳሜ እና እሁድ በየአካባቢው የሚቀርብ ሲሆን ÷ ድንች፣ ሽንኩርት፣ ቡና፣ ቲማቲም፣ ሀባብ እና ሌሎች ምርቶች ናቸው ለግብይት የሚቀርቡት።

በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች እና ሸማቾች መገኘታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.