መስፈርቱን ያላሟሉ ከ16 ቶን በላይ የምግብ ሸቀጦች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በመግቢያና መውጫ ኬላዎች በምግብ ምርቶች ላይ በተደረገ ቁጥጥር ከ16 ነጥብ 6 ቶን በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የምግብ ሸቀጦች የተቀመጠውን መስፈርት ባለማሟላታቸው ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ተደረገ።
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በመግቢያና መውጫ ኬላዎች ባሳለፍነው ሩብ ዓመት ከውጪ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ የተለያዩ የምግብ ምርቶች ላይ ቁጥጥር ማድረጉ ተገልጿል።
በዚህም 6 ሚሊየን 188 ሺህ 970 ቶን የምግብ ምርቶች እንደ ሩዝ ፣ ዱቄት፣ የህፃናት ወተት፣ የምግብ ጭማሪ እና የምግብ ጥሬ እቃዎች ላይ አስፈላጊውን የጥራትና ደህንነት ቁጥጥር በማካሄድ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ተደርጓል።
ሆኖም 16 ነጥብ 697 ቶን የሚሆኑ የተለያዩ የምግብ ሸቀጦች የተቀመጠውን መስፈርት ባለሟሟላታቸው ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ተደርጓል።
የምግብ ምርቶቹ በጉዞ ሂደት የተበላሹ፣ የጥራትና ደህንነት ችግር ያለባቸው መሆኑ በመረጋገጡ፥ ወደ አገር ውስጥ ገብተው ጥቅም ላይ እንዳይውሉ መደረጋቸውን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!