የሲሚንቶ ምርት መጠን እየጨመረ መሆኑን ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስታወቁ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲሚንቶ ምርትን ለማሳደግ መንግስት በዘርፉ ላይ በወሰደው የማሻሻያ እርምጃ የምርት መጠን እየጨመረ መሆኑን የማእድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስታወቁ።
ሚኒስትሩ በሙገር እና በዳንጎቴ የሲሚንቶ ፋብሪካ ተገኝተው የፋብሪካዎችን የምርት ሂደት ጎብኝተዋል።
የሲሚንቶ ምርትን ለመጨመር እየተሰራ ባለው የማሻሻያ ሥራም ሁለቱ ፋብሪካዎች በቀን የነበረው የምርት መጠናቸው በአሁኑ ወቅት እየጨመረ እንደሚገኝ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።
በተለይም የሲሚንቶ አምራቾች ለግብዓትነት የሚጠቀሟቸው ከውጭ የሚገቡ እንደ ድንጋይ ከሰል ያሉ የማዕድን ምርቶች ሙሉ ለሙሉ በሃገር ውስጥ ምርት ለመተካት እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።
“በቅርብ ጊዜም ይህ እቅድ በተግባር እንደሚገለጥ ጅምራችን ማሳያ ነው” ያሉት ኢንጅነር ታከለ ኡማ “በወሬው ወጀብ ሳንናወጥ ስራችንን በመስራት ባሰብነው ልክ ወደፊት መጓዛችንን እንቀጥላለን” ብለዋል።
በአዲስ ሙሉነህ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!