ሁላችንም የአገር መከላከያ ሰራዊት ነን – የጎዴ ከተማ ነዋሪዎች
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎዴ ከተማ ነዋሪዎች ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፋቸውን ለመግለጽ ሰልፍ አካሂደዋል።
በሶማሌ ክልል የተለያዩ ከተሞች የአገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፉ ሰልፎች እየተካሄዱ ሲሆን፥ የጎዴ ከተማ ነዋሪዎች ሁላችንም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ነን ሲሉም ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።
በሰልፎቹ ላይ ሁላችንም የአገር መከላከያ ሠራዊት ነን፣ ከአገር መከላከያ ሠራዊት ጎን ነን፣ አሸባሪው ትህነግ ዳግም እንዲመለስ አንፈቅም፣ የሚሉ መፈክሮችን በማሰማት በክልሉ ዞኖች ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂዷል፡፡
ነዋሪዎቹ የአሸባሪውን ትህነግ አስተሳሰብ እና ፍላጎት በሶማሌ ክልል ለማራመድ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንደሚታገሉ መግለጻቸውን የሶማሌ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!