Fana: At a Speed of Life!

የሆሳዕና ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ህወሓትን በመቃወም ሰልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የሆሳዕና ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች አሸባሪውን ህወሓት በመቃወም ሰልፍ አካሂደዋል።

በሰልፉ እኛ እያለን አሸባሪውና ወራሪው ቡድን አገራችንን አይበትንም ብለዋል ነዋሪዎቹ።

የአገራችንን ሉዓላዊነት ለማስከበር እስከ ህይወት መስዋዕትነት ከፍለን ግብዓተ መሬቱን እናፋጥናለን ሲሉም ገልጸዋል።

እስከ ግንባር ተጉዘን የዚህን አሸባሪ ቡድን ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋት ዝግጁ ነንም ብለዋል።

ጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት በዚህ አሸባሪ ቡድን ላይ እየወሰደ ባለው እርምጃ በድል እንዲመለስ የሚያስፈልገውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉም ነው የገለጹት።

የሆሳዕና ከተማ ከንቲባ አቶ አብረሃም መጫ፥ አሸባሪዎቹ ትህነግና ሸኔ በኢትዮጵያ ላይ የከፈቱትን ጦርነት በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት ሊዘምትበት ይገባል ነው ያሉት።

የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ ሎምቦሶ በበኩላቸው÷ ህወሓትን በአጭር ጊዜ ቀብረን አገራችንን ወደ ሰላም ለመመለስ የሚችል ሁሉ ወደ ግንባር በመትመም የማይችል ደግሞ የኋላ ደጀን በመሆን ተባብረን መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል።

ጀግናዉ የአገር መከላከያ ሰራዊት እየወሰደ የሚገኘውን አገርን የማዳን እርምጃ ለማጠናከር የዞኑ ህዝብ የሚያስፈልገውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግም አስረድተዋል።

በቢቂላ ቱፋ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.