Fana: At a Speed of Life!

የሀገርን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ የኢትዮጵያውያንን የአሸናፊነት ታሪክ ማስቀጠል ይገባል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገርን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ የኢትዮጵያውያንን የአሸናፊነት ታሪክ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ።
በቀደምት አባቶች አኩሪ ተጋድሎ ደምና አጥንት በጽኑ አለት የተገነባችው ኢትዮጵያ የተለያዩ ኃይሎች በሚፈጥሩት ውዥንብር የምትፈርስ አገር አይደለችም ብለዋል።
ለሀገር ሠላምና ደህንነት ከሕዝብ የተሰጠን ኃላፊነት በብቃት መወጣት እንደሚገባም ለምክር ቤቱ አባላት አሳስበዋል።
አባላቱ በቀጣይ ስራዎቻቸው አገራቸውንና ሕዝባቸውን በማገልገል ለተሰጣቸው ኃላፊነት ተግባራዊነት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም አፈ ጉባኤው አስገንዝበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.