የንግዱ ማህበረሰብ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ ወሰኑ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ የሀገር መከላከያ ሰራዊት 20 ሚሊየን ብር ለመለገስ ቃል ገቡ።
የንግዱ ማህበረሰብ ድጋፍ ለማድረግ ቃ የገቡት ዛሬ ከክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ ጋር በአገራዊ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ነው፡፡
በውይይቱ የተሳተፉ ባለሀብቶችም ሰላም ከሌለ ሰርቶ ማደር ስለማይቻል÷ ሰላማችንን ለማስጠበቅ ለሚዋደቀው መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
ከመንግስትና ከህዝብ ጋር በመሰለፍ በአገር ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመቀልበስ የድርሻንን እነወጣለን ሲሉም ነው ያረጋገጡት፡፡
የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ መስዋእትነት እየከፈለ ለሚገኘው ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ለሌሎች የጸጥታ ሃይሎች ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።
በውይይት መድረኩ 20 ሚሊየን ብር ለመለገስ ቃል ተገብቷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!