Fana: At a Speed of Life!

የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሁለተኛ ዙር ይሰጣል ተባለ

አዲ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሁለተኛ ዙር እንደሚሰጥ የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።
በ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከ600 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከ2ሺህ በላይ በሆኑ የፈተና ጣቢያዎች ለመፈተን መመዝገባቸውን የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ተናግረዋል፡፡
በሁለት ዙር ፈተናው እንደሚሰጥ ገልጸው÷ ከ90 በመቶ በላይ ተፈታኞች በመጀመሪያው ዙር ፈተናቸውን እንደሚወሥዱም አረጋግጠዋል፡፡
የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎችም÷ ሁለተኛው ዙር ፈተና ይሰጣል ብለዋል፡፡
ሁለተኛው ዙር ፈተናም በደቡብ ወሎ፣ ሠሜን ወሎ እና ዋግኽምራ ዞኖች እንደሚሰጥ ነው ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ያረጋገጡት፡፡
በሁለተኛው ዙር ፈተና የሚወሥዱ ተማሪዎች የሥነልቦና ግንባታና ክለሣ ተደርጎ ፈተና እንደሚወስዱም ገልጸዋል፡፡
በአማራ ክልል ከተለዩ ቦታዎች ውጪ በሌሎች አካባቢዎችም የሚለዩ ቦታዎች ካሉ በሁለተኛው ዙር ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ነው፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.