Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የሽብር ቡድኑን በሚደግፉ አካላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የአሸባሪውን ቡድን በገንዘብ፣ በፕሮፖጋንዳ እና በተለያየ መንገድ የሚደግፉ አካላት ላይ ጠንካራ ቁጥጥር እና ክትትል እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊሰ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ፖሊስ ኮሚሽኑ ከሌሎች ግብረሃይሎች እና ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ ባካሄደው ፍተሻና ብርበራ በርከት ያሉ የጦር መሣሪዎች መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ገልጸዋል፡፡
ከተያዙት የጦር መሣያዎች መካከልም÷ቦንብ፣ ፈንጂ እና ክላሽንኮብ ይገኙበታል።
በተጨማሪም÷ ለሽብር ቡድኑ ሊውሉ የነበሩ የተለያየ የጸጥታ ሃይል አልባሳት፣ የተያዩ ሃገራት ገንዘብ፣ የሃሰተኛ መታወቂያ መያዛቸውንም ኮሚሽነሩ አረጋግጠዋል፡፡
ከተማዋን ለማሸበር ከቡድኑ ትዕዛዝ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦችና የተለያዩ አካላት ተይዘው ምርመራ እተደረገ ነውም ተብሏል፡፡
ተጠርጣሪዎች ከየትም ወገን እና ብሄር ቢሆኑም÷ ጥቆማ ከደረሰ እና ሃገርን ብሎም ከተማዋን ለማወክ ከተሰማራ ይያዛል ለዚህም አስተማማኝ የጸጥታው እና የደህንነት ዘመቻ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
በፍሬሕይወት ሰፊው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.