Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የሽብር ቡድኖቹን ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ ሰልፍ ነገ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በነገው ዕለት አሸባሪዎቹን ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ እንዲሁም የሀገር ህልውናና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ አካላትን ለመደገፍ ህዝባዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ ከተማ አስተዳደሩ አሰታወቀ።
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ÷ ሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎች በነቂስ በመውጣት ሰልፉ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች መሳሪያቸውን እንዲያስመዘግቡ በቀረበው ጥሪ መሰረትም÷ እስካሁን ከ10 ሺህ በላይ የጦር መሳሪያ መመዝገቡም ተገልጿል።
አቶ ዮናስ በመግለጫቸው÷ ኢትዮጵያ በዘመናት መካከል የገጠማትን ፈተና በህዝቦቿ የተባበረ ክንድ አልፋልች፤ አባቶቻችን አልተንበረከኩም እኛም አንበረከክም ብለዋል፡፡
ሀገሪቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ እንደመሆኗ÷ ሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎች መታወቂያ፣ ፓስፖርት ይዘው መንቀሳቀስ አለባቸው ሲሉም አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣት ለመከላከያው ደጀን እንዲሆንና መከላከያውንም እንዲቀላቀል ኃላፊዉ ጥሪ አቅርበዋል።
በዘመን በየነ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.