ከ28 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ለማእከላዊ ገበያ እንደሚቀርብ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው የምርት ዘመን ከ28 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ለማእከላዊ ገበያ እንደሚቀርብ የቤንች ሸኮ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት መምሪያ ገለጸ፡፡
በአሁኑ ወቅት በዞኑ የቡና ምርት የመሰብሰብ ስራ ተጠናክሮ የቀጠሉን ጠቁመው÷ ምርቱም ከተጠበቀው በላይ ፍሬያማ መሆኑን የመምሪያ ምክትል ኃላፊና የቡናና ቅመማ ቅመም ጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ኪዳኔ ሺቅ ተናግረዋል፡፡
የአየር ሁኔታው የቡና ምርቱ ሳይባክን በጥራት ለመሰብሰብ መልካም አጋጣሚ መፍጠሩንም ገልጸዋል።
የፀጥታ ሁኔታው በሁሉም ቡና አምራች ቀበሌዎች የተሻሻለ በመሆኑ÷ በዞኑ ከተጠበቀው 28 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እንደሚያስችልም አቶ ኪዳኔ ገልፀዋል፡፡
በአደም አሊ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!