በመዲናዋ ነገ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ፖሊስ ይፋ አድርጓል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓት የጥፋት ቡድንን የሚያወግዝ እና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለመግለፅ ነገ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ የሚካሄድ መሆኑን ተከትሎ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል፡፡
የህወሓት የሽብር ቡድን እያካሄደ ያለውን ሀገር የማፍረስ ዓላማ ለመቃወም እንዲሁም የቡድኑን አባላት ህግ ፊት ለማቅረብ ሰራዊቱ እየወሰደ ያለውን እርምጃ ለመደገፍ ሰልፉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረሰ በመስቀል አደባባይ እና በዙሪያው የሚገኙ መንገዶች ለተወሰነ ሰዓት ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት፦
• ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ
• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን ላይና ታች
• ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት
• በቸርችልር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሐራምቤ ሆቴል
• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለገሃር መብራት
• ከሜክሲኮ አደባባይ ፣ በሰንጋ ተራ በድሉ ህንፃ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት
• ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ ተሽከርካሪዎች አጎና ሲኒማ ለቀላል ተሽከርካሪዎች ደግሞ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ
ነገ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሆኑ እና ከዛሬ ምሽት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ እና በዙሪያው ባሉ መንገዶች ተሽከርካሪ ለእረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!