ህውሓት ባለበት እንዲጠፋ ማድረግ ከክልሉ ህዝብ ይጠበቃል- የደቡብ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህውሓት ቡድን ዳግም ማንሰራራት እንዳይችልና ባለበት እንዲጠፋ ማድረግ ከመላው የክልሉ ህዝብ ይጠበቃል ሲሉ የደቡብ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡
ህወሓት የኢትዮጵያ ህዝብን የመበቀልና የማፍረስ አላማ ያለው በመሆኑ÷ የኢትዮጵያ ህዝብ በጋራ በመሆን ዘመቻውን በብቃት ተወጥቶና ጠላቶችን አንበርክኮ እስከወዲያኛው ለመሸኘት መረባረብ አለበት ብለዋል፡፡
መላው የክልሉ ህዝብም በአደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን በሰልፍ ከመግለጹ በተጨማሪ÷ በግንባር በመሰለፍ ቁርጠኝነቱን እያሳየ ነው፤ ይህም ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታልም ነው ያሉት፡፡
ከሀሰት መረጃዎችና ፕሮፖጋንዳ እራስን መጠበቅ ይገባል ያሉት ኃላፊው÷ እውነተኛ መረጃ ላይ መመስረት ከመከላከያ ጎን መቆምና አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
አካባቢን በመጠበቅና ሀገርን በማዳን ጥሪው ላይ በመሳተፍ ባጠረ ጊዜ ጦርነቱን አሸንፈን ወደ ልማት ለመመለስ መረባረብ ያስፈልጋልም ነው ያሉት፡፡
ከድጋፍ ስራ ጋር በተያያዘ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ ለመከላከያ ሰራዊቱ ማድረስ እንደተቻለና በቀጣይም እሩብ ቢሊየን ብር ለማሰባሰብ መታቀዱን ጠቁመው÷ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አብራርተዋል፡፡
በብርሃኑ በጋሻው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!