በአሶሳ ከተማ ህወሓትና ቅጥረኞቹን የሚያወግዝ ሰልፍ ነገ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሽባሪውን ህወሓትና ቅጥረኞቹን የሚያወግዝ እንዲሁም መንግሥት ሀገር ለማዳን የጀመረውን የህግ ማስከበር ዘመቻ የሚደግፍ ሰልፍ ነገ በአሶሳ ከተማ እንደሚካሄድ የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡
የድጋፍ ሰልፉ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ የፀጥታ መዋቅሩ አስፈለጊውን የቅደመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በአሶሳ ከተማና በዙሪያው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች አመራሮች፣ የመንግስት ሠራተኞች እንዲሁም የንግዱ ማህበረሰብ ከጥዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ በነቂስ በመውጣት ሀገር ለማዳን አጋርነታቸውን በድጋፍ ሰልፍ እንዲገልጹ የክልሉ መንግስት እና የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!