የሀገር ውስጥ ዜና

እኛ በሉዓላዊነታችን ተደራድረን አናውቅም – የአሰላ ከተማ ነዋሪዎች

By Feven Bishaw

November 07, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሰላ ከተማ አሸባሪዎቹን ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ አካላትን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡

የአሰላ ከተማ እና አከባቢዋ ነዋሪዎችም አሸባሪዉን የህወሓት እና ሸኔ ቡድን በማዉገዝ ከጠዋቱ 12 ሰአት ጀምሮ የተለያዩ መፈክሮችን በማንገብ በአሰላ አረንጎዴ ስታድየም ተገኝተዋል፡፡