Fana: At a Speed of Life!

በመስቀል አደባባይ የተካሄደው ህዝባዊ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል-ፖሊስ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢሲ)በመስቀል አደባባይ የተካሄደው ህዝባዊ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

“ሀገሬን እጠብቃለሁ መስዋዕትነት እከፍላለሁ” በሚል መሪ ቃል ህዝቡ ከመከላከያ ጎን መቆሙንና አሸባሪዎቹን ህወሃት እና ሸኔ ቡድኖች የሚያደርጉትን የጥፋት እንቅስቃሴ ለማውገዝ በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደው ህዝባዊ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ፕሮግራሙ በሰላም እንዲጠናቀቅ የከተማው ነዋሪ በተለይ ደግሞ የሰላማዊ ሰልፉ ታዳሚዎች ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ተገቢውን ትብብር ማድረጋቸውን ፣ ህብረተሰቡም የፀጥታው ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል አመለካከት በመያዝ ለፀጥታው ስራ ስኬታማነት የድርሻውን እየተወጣ እንደሆነ ፖሊስ አስታውሷል።

ነዋሪው እያበረከተ ላለው ቀና ትብብር እንዲሁም ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ ለሚገኙ መላው የፀጥታ አካላት እና የዛሬውን ሰልፉ ላስተባበሩና ለመሩ አካላት በሙሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ በፀጥታ አካላት ስም ምስጋናውን አቅርቧል።

የከተማውን ጸጥታ ለማስከበር በሚሰሩ ልዩ ልዩ ተግባራት ህብረተሰቡ እያበረከተ ያለውን አስተዋፆ አጠናክሮ እንዲቀጥልም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.