የሀገር ውስጥ ዜና

በአንዳንድ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ላይ የሚነዘው የሀሰት መረጃ ሊታረም ይገባዋል- አምባሳደር ሬድዋን

By Tibebu Kebede

November 07, 2021

 

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “አንዳንድ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ላይ በማታለልና በመዋሸት ዜና የሚሰሩበት አዝማሚያ ስር የሰደደ በመሆኑ ሊታረም ይገባዋል” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አሳሰቡ።

መገናኛ ብዙሃኑ ዘገባዎቻቸው ሚዛናዊና ሃላፊነት የተሞላባቸው መሆን እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት አስተያያት መገናኛ ብዙሃኑ በማታለልና በመዋሸት ዜና የሚሰሩበት አዝማሚያ ስር የሰደደ በመሆኑ መታረም እንዳለበት ገልጸዋል። “እውነት የሚሉትን ነገር ለመፈብረክና የሀሰት ዘገባዎችን ለማዘጋጀት ኢትዮጵያ ውስጥ መሆን አይጠበቅባቸውም” ብለዋል።

ከዚህ በኋላ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን “ለቅሷቸውንና ጩኽታቸውን” አቁመው ራሳቸውን በማረም በከፍተኛ የሃላፊነት ስሜትና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ዘገባዎቻቸውን መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!