በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የጂንካ ተወላጆችና የአማራ ወዳጆች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የጂንካ ተወላጆችና የአማራ ወዳጆች በአሸባሪውና ወራሪው የህውሓት ቡድን ከወሎ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ፡፡
ድጋፉ 760 ሺህ ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው ምግብና ቁሳቁስ መሆኑ ተመላክቷል።
የሸዋ ቀጠና የህልውና ዘመቻው አስተባባሪ ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው÷ በተለይ ወጣቱ ተፈናቅሎ ተረጂ ከመሆን ይልቅ የህልውና ዘመቻውን መቀላቀል እንዳለበት ተናግረዋል።
ተፈናቃዮቹ ለመዝመትና አሸባሪውን ወራሪው የህውሓት ቡድን ለመዋጋት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!