Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ እንደሚሠራ በተ.መ.ድ. የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ እንደሚሠራ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶክተር ካትሪን ሱዚ ገለጹ፡፡
አሸባሪው የህውሓት ቡድን በአማራ ክልል በከፈተው ወረራ በርካታ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመቶችን ፈጽሟል፤ እየፈጸመም ይገኛል ተብሏል፡፡
ንጹሀን የጦርነቱ ሰለባ ሆነዋል፣ ሕጻናት ሴቶች እና አረጋውያን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለከፋ ጉዳት ተዳርገዋል፡፡
ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም፣ በጊዜያዊነት ለመደገፍ እና የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ ከክልሉ እና ከፌዴራል መንግሥት አቅም ውጭ በመሆኑ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ በተደጋጋሚ ጥሪ ቀርቧል ነው የተባለው፡፡
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ÷ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶክተር ካትሪን ሱዚ ከተመራው የሰብዓዊ ድርጅቶች ልዑክ ጋር ዛሬ መክረዋል፡፡
በአሸባሪውና ወራሪው የህውሓት ቡድን የተፈናቀሉ ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር ውይይቶች እና ጥሪ ቀርቦ እንደነበር ያስታወሱት ርእሰ መሥተዳድሩ÷ በተግባር የተደገፈ ድጋፍ ግን የውይይቱን ያክል አልተገኘም ነው ያሉት፡፡
አሸባሪውና ወራሪው የህውሓት ቡድን ዓለም አቀፍ የጦርነት መርህን በጣሰ መልኩ ንጹሐንን የጦርነቱ ሰለባ አድርጓል፣ አፈናቅሏል፣ የሕዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን አውድሟል ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ፡፡
ለዚህ ሁሉ ጉዳት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሰጠው ተግባራዊ ምላሽ ግን የሚጠበቀውን ያክል አይደለም ነው ያሉት፡፡
በየጊዜው ውይይቶች መካሄዳቸው፣ የጉዳቱን መጠን መረጃ መሰብሰቡ እና ተቀራርቦ መሥራቱ መልካም መሆኑን አንስተው፥ ለችግሩ ስፋት የሚመጥን ተግባራዊ ምላሽ ማየት እንፈልጋለንም ብለዋል፡፡
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶክተር ካትሪን ሱዚ÷ ለችግሩ የሚመጥን የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ በተደጋጋሚ ቃል መገባቱን ገልጸው ÷ ርእሰ መሥተዳድሩ ያነሱት የተግባራዊ ምላሽ ጥያቄ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡
የጦርነቱ ሂደት መራዘም፣ የተጎጂዎች ቁጥር በየጊዜው መጨመር እና ንጹሐን የጦርነቱ ሰለባ መሆናቸው በድጋፍ አቅርቦቱ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯልም ብለዋል፡፡
የተደረገው ድጋፍ ከተፈጠረው ችግር አንፃር አናሳ ቢሆንም ሙከራዎች መኖራቸውን ያነሱት ዶክተር ካትሪን÷ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ተቋቁሞ ድጋፍ ለማድረስ ድርጅታቸው እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡
የትምህርት፣ የጤና እና የውኃ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ድጋፍ ለማድረግ በየጊዜው መረጃ እየተሰበሰበ ነው ብለዋል ዳይሬክተሯ፡፡
የዓለም ምግብ ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ስቴቨን ዎሬ ኦማሞ÷ በሽብር ቡድኑ በተወረሩ አካባቢዎች ላሉ እና አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረስ በኢትዮጵያ በቂ የምግብ ክምችት እንዳለው ገልጸዋል፡፡
ለአቅርቦቱ ችግሮች ያሏቸውን ምክንያቶች ለርእሰ መሥተዳድሩ አቅርበዋል፡፡
“በተወረሩ አካባቢዎች አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ ህወሓት እንቅፋት ሆኖብናልም” ነው ያሉት ስቴቨን ዎሬ ኦማሞ፡፡
የሚላከው የምግብ ድጋፍ ቀጥታ ለተጎጂዎች መድረሱን ማረጋገጥ አለመቻሉን፣ የምግብ ድጋፉን ለማድረስ የትራንስፖርት እና የፀጥታ ስጋት ችግሮች እንዳሉ አንስተዋል፡፡
በቀጣይም ከፌዴራሉ እና ከክልሉ መንግሥት ጋር ተቀራርቦ ችግሩን ለመፍታት እንደሚሠራም ገልጸዋል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ካትሪን ሱዛን እና ልዑካቸው በዘንዘልማ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች መጎብኘታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People reached
65
Engagements
Boost Post
62
1 Comment
2 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.