Fana: At a Speed of Life!

ሕዝብ ተናግሯልና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሊያዳምጥ ይገባል -የመንግሥት ኮሙኒኬሽን

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝብ ተናግሯልና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሊያዳምጥ ይገባል ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ፥ ሰሞኑን በተለያዩ ክልሎች ከ30 ሚልየን በላይ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ ስለሀገሩ ተናግሯል ተናግሯል ብሏል።
ኢትዮጵያን ለማዳን እስከ ሕይወት መሥዋዕትነት እንደሚከፍል፣ ለጸጥታ ኃይሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ፣ ማንኛውንም የውጭ ጣልቃ ገብነት እንደማይቀበል፣ የሕወሐትንና አጋር ጽንፈኛ ኃይሎችን ሀገር የማፍረስ የሽብር ተግባራት አጥብቆ እንደሚያወግዝ በግልጽ ተናግሯል ነው ያለው ።
እንዲሁም አንዳንድ የውጭ ሚዲያዎች፣ ዲፕሎማቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ስለ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፉትን የተዛባ መረጃ ሕዝቡ ኮንኗል።
የሚያስተዳድረውን መንግሥት ነጻ፣ ገለልተኛና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መምረጡንና ይህንን ውሳኔውንም ዓለም እንዲያከብርለት ሕዝቡ አጥብቆ ጠይቋል።
ሕዝቡ ሀገሩን ለማዳን ማንኛውንም መሥዋዕትነት እንደሚከፍል በተግባር አሳይቷል ሲል ገልጿል።
ሕዝቡ በወራሪው በተያዙ አካባቢዎችም በከፍተኛ ግለት እየተነሣ ነው።
በተወረሩ አካባቢዎች የሚገኘው ሕዝብ ጽንፈኛውን ህወሓት ምቾት ተሰምቶት እንዳይቀመጥ እያደረገው ይገኛልም ነው ያለው።
ይህ የሕዝብ ንቅናቄ አሸባሪውን በሁሉም ቦታዎች እግር በእግር እየተከታተለ ርምጃ በመውሰድ አካባቢዎችን ተገድዶ እንዲለቅ እያደረገው ይገኛል ሲል ገልጿል።
አሁን የተጀመረውን ለኢትዮጽያ ህልውና ሕዝብን የማዝመት ንቅናቄ በብዛትና በስፋት በማከናወን፣ አሸባሪውን ሕወሐትን ድል ማድረግ እንዳለበት ሕዝቡ በአንድ ቋንቋ ተናግሯል ብሏል።
ግንባር ቀደም ሆኖ እንደሚዘምትም አረጋግጧል። ወሳኙ ጉዳይ የውስጥ ዐቅማችንን መጠቀም መሆኑን ሕዝቡ በአደባባይ አሳይቷል ነው ያለው።
ሕዝብ ተናግሯልና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሊያዳምጥ ይገባልም ነው ያለው።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.