በሀገሪቱ የተቃጣውን ጥቃት ለመመከት ከመንግስትና ከመከላከያ ሰራዊት ጎን መቆም ይገባል – የጉራጌ ዞን ነዋሪዎች
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃገሪቱ የተቃጣውን ጥቃት ለመመከትና አሸባሪውን ወራሪ የህውሓት ቡድን ለመደምሰስ የኢትዮጵያ ህዝብ ከመንግስትና መከላከያ ሰራዊት ጎን መቆም ይገባዋል ሲሉ የጉራጌ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ።
ነዋሪዎቹ አሸባሪውን ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ፣ ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።
የዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ጀማል÷ ኢትዮጵያ ለዘመናት የተወዘፈውን የህብረተሰቡ የዲሞክራሲ እጦት ጥያቄ ምላሽ መስጠት የተጀመረበት በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ለመበታተን የውስጥና የውጭ ጠላቶችዋ የህልውና አደጋ የደቀኑበት ወቅት ላይ ትገኛለች ብለዋል።
አሸባሪዎቹ የህወሓት ቡድንና ሸኔ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ያልተገባ ጋብቻ ፈጽመዋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው÷ ይህንን ለመመከት ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እኛ እያለን ሀገር አትፈርስም፣ ይልቁንም ሽብርተኞቹን ለአንዴና ለመጨረሻ ግብዓተ ቀብራቸውን በመፈጸም የሀገሪቱን አንድነት በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም ከጫፍ እስከ ጫፍ ተነስቷል።
የጉራጌ ዞን ማህበረሰብ በሀገሪቱ የተቃጣውን ጥቃት ለመመከት ከመንግስትና ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም ከ67 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል።
ወጣቱ ወደ ግንባር በመዝመት፣ አቅም የሌለው ገንዘብ በመለገስ፣ስንቅ በማዘጋጀት፣ሞራል በመስጠት፣ ጸሎት በማድረግ እንዱሁም ተደራጅቶ የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ በመጠበቅ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል።
የኢዜማ አስተባባሪና የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ በበኩላቸዉ÷ አሸባሪውና ወራሪው የህውሓት ቡድን ኢትዮጵያን በብሄርና በጎሳ ከፋፍሎ የቀበረውን የጥላቻ ቦንብ በማፈንዳት እንዲሁም በጥቅም በገዛቸው ባንዳዎች አማካኝነት ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው የመጣን ጠላት ለመመከት እራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡ ኩሩ ህዝቦች ያሉባት ሀገር ናት ያሉት አቶ ደምስ÷ አቅሙ የሚፈቅድለት የዞኑ ህዝብ በሙሉ ሀገሪቱን ለመበታተን የተነሳውን ሰይጣን ወደ ሲኦል ለመሸኘት ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ሀገር የማዳን ግዴታውን እንዲወጣ ጥሪ ማቅረባቸውን ከጉራጌ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!