የሀገር ውስጥ ዜና

የ2012 ሃገር አቀፍ ፈተና የመስጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ሆነ

By Tibebu Kebede

February 10, 2020

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2012 የትምህርት ዘመን ሃገር አቀፍ ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳን ይፋ አድርጓል።

በዚህ መሰረት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 24 እስከ ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል።

ከዚህ ባለፈም የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ደግሞ ከሰኔ 1 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥም ኤጀንሲው አስታውቋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision