ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቻይና የኮቪድ-19 መከላከያ መመሪያዎቿን እስከ2022 ልትቀጥል ነው

By Melaku Gedif

November 08, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ቻይና ኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር  ያወጣቻቸዉን መመሪያዎች እስከ 2022 ድረስ ተግባራዊ እንደምታድርግ አስታወቀች።

በሀገሪቱ ብሔራዊ ጤና ጥበቃ ኮሚሽን የበሽታዎች መቆጣጠሪና መከላከል መምሪያ  ምክትል ኃላፊ ዡዉ ሊያንጉ በቤጂንግ በተካሄደው ኮንፈረንስ ላይ  እንደተናገሩት፥  ቻይና ጥብቅ የኮቪድ -19 ፖሊሲዎችን እስከ ሚቀጥለው 2022 ድረስ ታስቀጥላለች፡፡

በቅርቡ በመላ አገሪቱ በተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ላይ ፈጣን እርምጃዎች ለመውሰድና የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል እንዲቻል ውሳኔ መተላለፉን  ነው ምክትል መምሪያ  ኃላፊው የገለጹት።

ሀገሪቱ ከጥቅምት 17 እስከ ህዳር  5 ባሉት ቀናት  በ20 ግዛቶቿ ውስጥ በሚገኙ 44 ከተሞች 918  አዲስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ዜጎች  ማስመዝገቧ ተገልጿል።

በሀገሪቱ 20 ሚለየን ዜጎች የኮሮና ቫይረስ ክትባት የወሰዱ ሲሆን፥  ህፃናትን ጨምሮ ክትባቱን ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የሀገሪቱ የጤና ባለሙያዎች እየሰሩ መሆኑ ተመላክቷል ሲል ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

 

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

 

መከላከያን ይደግፉ!

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

 

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!